1771461377343756

ነገን ዛሬ እንትከል

ዝግጁ ናችሁ!! እኛ ዝግጅታችንን ጨርሰናል።  ኢትዮጵያም ታሪክ ለመስራት ተዘጋጅታለች  500 ሚሊዮን ችግኞች ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ ድረስ ምድራችንን በልምላሜ እንሞላዋለን!!  ከጋምቤላ እስከ ጅግግጋ ጫፍ ድረስ 🇪🇹 በነቂስ ወጥተን ሀያልነታችንን ለአለም እናሳያለን!!  ሀምሌ 10 አንድም ሰው ፈፅሞ ከቤቱ አይቀርም!!  ህፃን፣አዋቂ፣ጎልማሳ ሳንል በአንድ ላይ ዘምተን አረንጓዴ አሻራችንን እናሳርፋለን 🇪🇹 2ኛውን ዙር ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መረሃ-ግብር ከጫፍ ጫፍ በአንድነት ተምመን ችግኞችን በመትከልና የተከልናቸውን በመንከባከብ ደማቅ ታሪክ ፅፈን ለቀጣይ ትውልድ አረንጓዴ ኢትዮጵያን እናስረክባለን!! ዛሬን በታማኝነትና በህዝባዊነት መርህ ህዝባችንን እያገለገልን፤ የነገዋ ኢትዮጵያ ለነገዎቹ ሀገር ተረካቢ ትውልዶች አንድነትና ቀጣይነት የተመቻቸች እንዲትሆን አረንጓዴ አሻራችንን በደማቅ እንፅፋለን! ችግኛችን መትከልና መንከባከብ ለነገ ሀገር ተረካቢ ትውልዶች መሰረት መጣል ነው! ለነገ ሀገር ተረካቢ ትውልዶች ነገያቸውን ዛሬ ሰርተን፤ ቀጣዩ ትውልድ ለቀጣዮቹ ትውልዶች መሰረት እንዲሆኑ አኛዎቹ ዛሬዎች ዛሬን ለነገ እንኑር!! አረንጓዴ አሻራችንን አያኖርን ፣ ችግሮቻችንን በሰላማዊ መንገድ እየፈታን #የኢትዮጵያን እድገት እና ብልፅግናን እናረጋግጣለን!  #ኢትዮጵያን_እናልብሳት🌲🌲🌳#አረንጓዴ_አሻራ🌴🌳🌲#Green_Legacy🌲🌳 ሰላም ፣ ፍቅር፣ ልማትና ብልፅግና ለኢትዮጵያችን ይሁንልን!!! መልካም የስራ ቀን ተመኘን!@lideta prosperity party_ብልፅግና

1771215797559909

ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም ጀንበር ወጥታ እስክትገባ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ቤቱ አይውልም

“ከተደመርን በሁሉም መስኮች ኢትዮጵያዊያን ያሰብነውን ማሳካት እንደምንችል አምናለሁ፡፡ ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም ጀንበር ወጥታ እስክትገባ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ቤቱ አይውልም፡፡ በዕቅፍ ካለ ሕጻን፣ በድካም ካለ አረጋዊ፣ በአልጋ ከሚገኝ ታማሚ በስተቀር ቤቱ ማንም አይውልም፡፡ ምክንያቱም ይህ የፖለቲካ ጉዳይ አይደለም፤ የፓርቲ ፕሮግራምም አይደለም፤ የመንግሥት ጉዳይም አይደለም፡፡ ይህ የኢትዮጵያ ጉዳይ ነው፡፡ የምትለብሰው ኢትዮጵያ ናት፡፡ ትርፉም ከእኛ አልፎ ለዓለም የሚተርፍ ነው፡፡ ስለዚህም የእምነትና የባህል፣ የፖለቲካ ፓርቲና አስተሳሰብ፣ እድሜና ጾታ፣ የትምህርትና የኑሮ ደረጃ ሳይለየን ሐምሌ 10 ቀን ከጀንበር ቀድመን እንውጣ፡፡ ከጀንበር በኋላ እንመለሳን፡፡ ኢትዮጵያን አረንጓዴ እናለብሳለን፡፡” – የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር)

1771684578027580

እንኳን ደስ አለን! ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር ከ500 ሚሊየን በላይ ችግኝ መትከል ችላለች!

ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር ከ500 ሚሊዮን ችግኝ በላይ መትከል ችላለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከሁነቶች መከታተያ ክፍል ባደረሱት መልዕክት ከጠዋት 12 ሰአት እስከ ማታ 12 ስአት ድረስ በተካሄደው የችግኝተከላ መርሃ ግብር  ከ500 ሚሊየን ችግኝ በላይ መተከል መቻሉን አስታውቋል።