የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ዓላማዎች
የብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራም በህዝቡ ውስጥ ሰርፆና ተግባራዊ ሆኖ መላው የአገራችን ሴቶች ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ
ሴቶች በዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ በማድረግ በየደረጃው የልማት የዴሞክራሲና የሰላም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል
ሴቶች ህገ-መንግስቱ ያጎናፀፋቸውን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በትክክል ስራ ላይ እንዲውሉ ጠንካራ አደረጃጀት በመፍጠር ለመብታቸው እንዲታገሉ ማስቻል
የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ የሴቶችን አቅም በመገንባትና የሴቶች እኩልነት የሚገድቡ ባህላዊና ልማዳዊ ተጽዕኖዎችን በመለየት ለሀገር ዕድገት እና በሴቶች ላይ የሚፈጠሩትን ተጽዕኖ በማስገንዘብ እንዲወገድ በማድረግ ሴቶች በውሳኔ ሰጪነት እኩል እንዲሳተፉ
ሴቶች የፈጠራ ዝንባሌያቸው እንዲጎለብት፣ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እና የስራ ባህላቸው ዳብሮ ስራ ፈጣሪ በመሆን እራሳቸውን እና ሀገራቸውን ከድህነት ለማውጣት የሚታገሉ እንዲሆኑ ማድረግ
ሴቶች ህብረ ብሄራዊ አንድነታቸውን በመጠበቅ የመተሳሰብና የመረዳዳት ባህል በማጎልበት በሀገራዊ ጉዳዬች ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ማስቻል
የብልጽግና ሴቶች ሊግ መርሆዎች
የብልጽግና ሴቶች ሊግ መርሆዎች የሚከተሉት ናቸው
ህዝባዊነት
ዳሞክራሲያዊነት
የህግ የበላይነት
ልማትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት
ተግባራዊ እውነታ
ሀገራዊ አንድነትና ህብረ-ብሄራዊነት
የብልጽግና የሴቶች ሊግ እሴቶች
የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ እሴቶች ይኖሩታል
እህታማማችንት
መካባበር መቻቻል
ህብረብሄራዊ አንድነት
የዜጎች ክብርና የስርዓት ፅታ እኩልነት
ነፃነት
እኩል ተሳትፎ ና ፍትሀዊ ተጠቃሚነት