የኮሚሽኑ ተግባራትና ኃላፊነት
የፓርቲውን ህይወት መጠበቅ
ሀ) የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብና መመሪያዎች በሥራ ላይ መዋላቸውን መከታተል
ለ) የፓርቲውን የፖለቲካ ጥራትና የሥነምግባር ጤናማነት ለማረጋገጥ ክትትል ማድረግ
ሐ) የፓርቲ ሥነ ምግባርን ያሻሽላል፣ ሙስናን ለመዋጋት ጥረቶችን ማድረግ፣ ማስተባበር
መ) የሥነ ምግባር ጥሰቶችን መመርመር፣ ተገቢውን የእርምት ርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ
ሠ) ከፓርቲው አስተባባሪ ኮሚቴዎች በሚሰጥ ተልእኮ ምርመራ፣ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ
ረ) በፓርቲው አካላት መካከል ልዩነት ሲኖር ወይም መጣራት የሚገባቸው ጉዳዮች ሲኖሩ እንዲሁም በፓርቲው ማ.ኮ/ሥአኮሲጠየቅ አጣርቶ የውሳኔ ሀሳብ ሪፖርት ለማ/ኮሚቴ ያቀርባል
የፓርቲውን አባላት መብት መጠበቅ
ሀ) የፓርቲው አባላትና አካላት መብቶች እና ጥቅሞች መከበራቸውን ይከታተላል
ለ) ከአባላት የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ይቀበላል፣ ይመረምራል፣ የእርምት የውሳኔ ሐሳቡን ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና እንደ አግባቡ በየደረጃው ላሉ የፓርቲ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ያቀርባል
ሐ) ፓርቲው ርምጃ የተወሰደበት አባል/ዕጩ አቤቱታውን በየደረጃው ላለው የፓርቲ መዋቅር አቅርቦ ካልረካ በየደረጃው ላለው ኮሚሽን ሊያቀርብ ይችላል
የፓርቲውን ሀብቶች መቆጣጠር
ሀ) የፓርቲዉ፣ ገንዘብ፣ ንብረትና ሰነዶች በአግባቡ መጠበቃቸውን ቁጥጥር ያደርጋል፣ የፓርቲው አባላት መዋጮ በወቅቱና በትክክል መሰብሰቡን ይቆጣጠራል፡፡
የኮሚሽኑ የውስጥ አሠራሮች
ሀ) ዝርዝር የሥነ ምግባር፣ የኢንስፔክሽንና የቁጥጥር መመሪያ በማርቀቅ ለፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አቅርቦ ያጸድቃል፣ ተፈጻሚነቱን ይከታተላል
ለ) ኢንስፔክሽንና ልዩ ልዩ ጥናቶችን ያካሂዳል፣ የጥናቱን ግኝቶች ከውሳኔ ምክረ ሐሳብ ጋር ለሚመለከታቸው የፓርቲ አካላት ያቀርባል፣ አፈፃፀሙንም ይከታተላል
ሐ) ለሥራ የሚያስፈልገውን ዓመታዊ በጀት በማዘጋጀት እንዲፀድቅ ለማዕከላዊ ኮሚቴ ያቀርባል፣ ሲፀድቅ ያስተዳድራል፣ ይመራል፤
መ) ለፓርቲው ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ተገዢ ያልሆኑ የኮሚሽኑ አባላትን በ2/3ኛ ድምጽ ያግዳል
ሠ) ስለሥራው ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት ያቀርባል
ረ) የኮሚሽኑን የውስጥ የአሰራር መመሪያዎች ማውጣት ይችላል