
ኢትዮጵያ የወጣቶች ሀገር ናት በታሪኳ ተከብራ የኖረችው በወጣቶች ግንባር ቀደም መሪነት እና ተሳትፎ ነው.የኢትዮጵያ ወጣቶች ለውጡን ለመፍጠር ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍለናል በለውጡ ሂደት በተመዘገቡ ድሎች ውስጥ የማይተካ ሚና ተጫውተናል. በለውጡ ዘመን ሊጋችን በየደረጃውና በየዘርፉ በተለይም በበጎ ፍቃድ ስራ ጀምሮ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ያመነጯቸውን በርካታ የብልፅግና ሀሳቦች ተግባራዊ ለማድረግ እጅግ አመርቂ ርብርብ አድርገናል እንደ ክፍለ ከተማችንም በርካታ ተግባራትን በስኬት አጠናቀናል. ውድ የክፍለ ከተማችን ወጣቶች ኢትዮጵያ ደምቃ የምናያት ግን በምኞት ሊሆን አይችልም በወጣቶች የምትሰራ የተሻለች ኢትዮጵያን ነገ ለማየት ዛሬ አንድ ሆነን መቆም አለብን። አንድ ሆነን መቆም የምንችለው በሊጋችን ግንባር ቀደም ትግልና መሪነት ህብረታችንን የሚሸርብሩ ፅንፈኝነት፣ዘረኝነት፣ሌብነትን የመሰሉ ተሻጋሪ ህመሞችን ዛሬውኑ መታከምና መዳን ስንችል ነው።ለዚህ ወሳኝ ትግል እንትጋ።