ለፀጥታ አካሉ የበሬ ስጦታ ያበረከቱት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ የሠላምና ፀጥታው አካል በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሠላም እንዲጠናቀቅ እያደረጉ ያለው ተግባር እጅግ የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው በዓሉ የሠላምና የደስታ እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
የለሚ ኩራ ኮሚኒኬሽን
ታህሳስ 28/2017 ዓ.ም









ለፀጥታ አካሉ የበሬ ስጦታ ያበረከቱት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ የሠላምና ፀጥታው አካል በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሠላም እንዲጠናቀቅ እያደረጉ ያለው ተግባር እጅግ የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው በዓሉ የሠላምና የደስታ እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
የለሚ ኩራ ኮሚኒኬሽን
ታህሳስ 28/2017 ዓ.ም
በእለቱ በስፍራው በመገኘት የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብሩን ያስጀመሩት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ እንዳሉት በዓሉ የአንድነት የፍቅር የመተሳሰብ የአብሮነት እንዲሆን እየተመኘው ያላችሁን ማንኛውንም ጥያቄዎች የክፍለ ከተማ አስተዳደሩ ደረጃ በደረጃ ፈጣን ምላሽ እንደሚሠጥም ገልፀዋል።
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፈንታሁን ሌማንቾ አክለው በዓሉን በእህታማማችነትና ወንድማማችነት መንፈስ ያለንን እየተጓደስ በጋራ እየተባበርን በአንድነት በዓሉ እናክብር ሲሉ መልካም የገና በዓልም እንዲሁም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
የለሚ ኩራ ኮሚኒኬሽን
ታህሳስ 28/2017 ዓ.ም
በምዘናው በተግባራት አፈፃፀም የታዩ ጥንካሬዎችን የማስቀጠልና ክፍተቶችን በማረም ለተሻለ ውጤታማ ስራ እውን መሆን አቅም ለመፍጠር ያለመ እንደሆነም ተገልጿል።
የለሚ ኩራ ኮሚኒኬሽን
ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የስራ ዕድል ፈጠራ፣ የልማት ትሩፋት የንቅናቄ ስራ እና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ቀጣይ በሚተገበረው የምግብ ዋስትና ፕሮግራም የተጠቃሚዎች ልየታ፣ የደረጃ ፍረጃ እና የ2ኛ ዙር ተጠቃሚዎች ምርቃት ተገምግሞ የስራ አቅጣጫ ማስቀመጡንም ገልጿል።
መድረኩን የመሩት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፈንታሁን ሌማንቾ እንዳሉት ተግባራቱን አመራሩ ትኩረት በመስጠት በከፍተኛ እርብርብና ቅንጅት ሊሠራ ይገባል ሲሉ አክለው አመራሩ የተለያዩ የንቅናቄ እና ሰው ተኮር ስራዎችን አቀናጅቶ የመምራት አቅሙን ተጠቅሞ ወጣቶችን ሴቶችን እና ሌላውን የህብረተሰብ ክፍል በማሳተፍ የሌማት ትሩፋት ስራውን በከፍተኛ እርብርብ መስራት ይኖርበታልም ብለዋል።
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ልመንህ ምህረቱ አክለው እንዳሉት ከሥራ ዕድል ፈጠራና ከሌማት ቱሩፋት የንቅናቄ ሥራዎች አንፃር የአፈፃፀም ሂደቱን አጠናክሮ መቀጠል ጥራቱን በሱፐርቪዥንና ድጋፍ በማድረግ ሥራዎችን ተሳስሮ እንዲቀጥል የአመራር ትኩረት ይፈልጋል ሲሉ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ተግባራዊ በሚደረገው የከተማ ምግብ ዋስትና እና ልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎችን ለመለየት የምዝገባ ሥራው መጠናቀቁ በመድረኩ በጠንካራ ጎን የተነሳ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናት ተመዝጋቢዎችን በደረጃ የመፈረጅ ሥራውን በማጠናቀቅ ለማህበረሰቡ ማስተቸት እንደሚገባ አቅጣጫ ሠጥተዋል።
የለሚ ኩራ ኮሚኒኬሽን
ታህሳስ 13/2017 ዓ.ም
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት የሴት አመራሮችን አቅም ለማጎልበት በሴቶች ውሳኔ ሰጭነት እና የአመራር ብቃት ስልጠና መሰጠቱ ተገልጿል፡፡
በመድረኩ ላይ ተገኝተው የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሪት ወይንሸት አስናቀ ስልጠናው ጥሩ መነሳሳና ቁጭትን የሚያጭር ነው ያሉ ሲሆን የሰለጠነውን ስልጠና ወደ ተግባር ቀይረን በህይወታችን ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ሙሉ እመቤት ስራህ ብዙ የሴቶችን የአመራርና የውሳኔ ሰጭነት አቅም ለማጎልበት ከተቀመጡ የልማትና የለውጥ ፓኬጆች አንዱ የሴቶችን ውሳኔ ሰጭነትና የአመራር ብቃት ማሳደግ መሆኑን ገልጸው በሴቶች ውሳኔ ሰጭነት እና የአመራር ሚና ዙሪያ ከወረዳ እስከ ክ/ከተማ ለሚገኙ ሴት አመራሮች ስልጠና መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡
ወ/ሮ ሙሉእመቤት ሴቶች የሀገር ዋልታና መሰረት በመሆናቸው በተለያየ ደረጃ በሚገኙ የአመራርነት ማዕቀፎች ማሳተፍ እና የአመለካከት ለውጥ ማምጣት ሲቻል መሆኑን ገልጸው ሴቶች ከቤተሰብ ጀምሮ በየትኛውም የስልጣን ደረጃ መሳተፍ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
via ለሚ ኩራ ኮሚዩኒኬሽን
ታህሳስ 22/2017
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ፅ/ቤት ከክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ጋር በመሆኑ ህብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነት /እህታማማችነት ለሁለንተናዊ ብልፅግና ” በሚል መሪ ቃል ከመምህራን ጋር የፓናል ውይይት አካሂዷል
በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ እንደተናገሩት መምህራን ሀገርን በመገንባት ሂደት ዋጋቸው ከፍ ያለና ትውልድን በእውቀትና በመልካም ስነ -ምግባር በመገንባት ትልቅ ሚና እንዳላቸው በመግለፅ የመድረኩ ተሳታፊዎች ገዥ ትርክት ህዝቦችን ከህዝቦች የሚያቀራርብ መሆኑን መገንዘብ ፣ህብረ -ብሔራዊ ወንድማማችነት/እህታማማችነት ያለውን ፋይዳ መረዳትና ለትውልድ በደንብ ማስተማር ለሀገር እድገት እና ብልፅግና በጋራ መቆም እንዲሁም የተጀመረውን ዜጎችን በጥሩ ስነ-ምግባር የመገንባት ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥሉ አሳስበዋል ።
የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ሌማንቾ በበኩላቸው ብልፅግና ጉዞአችን ለማፅናት ገዥ ትርክት አስፈላጊ በመሆኑ በትውልድ ግንባታ ላይ ከፍተኛ ሚና ያላቸው መምህራን በአሰባሳቢ ትርክት ዙሪያ ያለውን ግንዛቤ ከፍ በማድረግ ሀገርን በጋራ ለመገንባት በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
ለፓናል ውይይት መነሻ ፅሑፍ ያቀረቡት በብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ /ጽ/ቤት ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳዊት ምንዳዬ እንደገለፁት ገዢ ትርክት አሳባሳቢ፣ አብሮነታችንን የሚያፀና ፣ብሔራዊነት ለሁሉም እኩል ዕድል ፣በአስተሳሳሪ ነገ ላይ መገንባት የሚሰጥ ስለሆነ ገዢ ትርክትን በማፅናት መምህራን በትልውድ ግንባታ ላይ ያላቸውን አዎንታዊ ሚና መወጣት ያስፈልጋል ብለዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው መድረኩ በጣም አስፈላጊና ህብረ -ብሔራዊ ወንድማማችነት /እህታማማችነት እሴት የበለጠ ለማጠናከር የተሻለ ግንዛቤ ያገኙበት መሆኑን ገልፀው በቀጣይም የጋራ ግንዛቤ የሚያስጨብጡን ተመሳሳይ መድረኮች መዘጋጀት ይገባል ብለዋል።
ለሚ ኩራ ኮሙኒኬሽን
ታህሳስ 19/2017 ዓ.ም
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም የገና በዓል ባዛር ዝግጅ የካ አቦዶ መስቀለኛ አደባባይ የከተማና ክፍለ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በይፋ ተከፍቷል ።
ባዛሩ ገበያን የማረጋጋትና ለአምርራች ኢንዳስትሪዎች የገበያ ትስስር የሚፈጥር ዓላማ በመያዝ በክፍለ ከተማው ስራ እና ክህሎት ፅ/ቤት ፣ ህብረት ስራና ኢንዱስትሪ ልማት ፅ/ቤቶች በቅንጅት መዘጋጀቱ ተገልጿል ።
ፕሮግራሙን መርቀው የከፈቱት የለሚ ኩራ ክፍለ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ እንደገለፁት በመጪው ገና በዓል የኢንዱስትሪናግብርና ምርቶችን በበቂ ሁኔታ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ከፍተኛ ዝግጅት መደረጉን ገልፀው ሸማቹ ህብረተሰብ ምርቶችን በጥራት በአቅራቢያቸው እንዲያገኙ የሚያስችል የተለያዩ መሸጫ ቦታዎች በማዘጋጀት የምርት አቅርቦቱ በብዛትና ጥራት እንዲቀርብ በክፍለ ከተማችን ያሉ የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራትና ዩኒየኖች ከክልሎች ዩኒየኖችና የገበሬ ህብረት ስራ ማህበራት ጋር የማስተሳሰር ስራ በመሰራት በዋናነት
ለበዓሉ የሚሆኑ ዶሮ፣እንቁላልና ሌሎች ምርቶች በስፋት የማቅረብ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል ።
በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍሰሐ ጥበቡ በመልክታቸው በመጪው ገና በዓል ገበያውን ለማረጋጋት እንደ ከተማ ሰፊ ዝግጅት መደረጉን ገልፀው አምራቾች ፣አርሶ አደሮችና ህብረት ስራ ማህበራትን በመጠቀም የግብርና ኢንደስትሪ ምርቶችን በስፋት በማቅረብ ገበያውን የማረጋጋት ስራ በስፋት ተስርቷል ብለዋል።
የገበያ መዳረሻዎችን የማስፋፋት ፣የምርት አቅርቦቱን የመጨመር እና ቁጥጥርና ክትትል ስራዎችን በማጠናከር በበዓሉ ወቅት ምንም አይነት የምርት እጥረት እንዳይኖር እየተሰራ መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል።
በመጨረሻም የለሚ ገበያ ማዕከል የግብርና እና ኢንዱስትሪ ምርቶች አቅርቦት ያለበት ደረጃ ጉብኝት አድርጓል ።
ለሚ ኩራ ኮሙኒኬሽን
ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም
ዝግጁ ናችሁ!! እኛ ዝግጅታችንን ጨርሰናል። ኢትዮጵያም ታሪክ ለመስራት ተዘጋጅታለች 500 ሚሊዮን ችግኞች ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ ድረስ ምድራችንን በልምላሜ እንሞላዋለን!! ከጋምቤላ እስከ ጅግግጋ ጫፍ ድረስ 🇪🇹 በነቂስ ወጥተን ሀያልነታችንን ለአለም እናሳያለን!! ሀምሌ 10 አንድም ሰው ፈፅሞ ከቤቱ አይቀርም!! ህፃን፣አዋቂ፣ጎልማሳ ሳንል በአንድ ላይ ዘምተን አረንጓዴ አሻራችንን እናሳርፋለን 🇪🇹 2ኛውን ዙር ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መረሃ-ግብር ከጫፍ ጫፍ በአንድነት ተምመን ችግኞችን በመትከልና የተከልናቸውን በመንከባከብ ደማቅ ታሪክ ፅፈን ለቀጣይ ትውልድ አረንጓዴ ኢትዮጵያን እናስረክባለን!! ዛሬን በታማኝነትና በህዝባዊነት መርህ ህዝባችንን እያገለገልን፤ የነገዋ ኢትዮጵያ ለነገዎቹ ሀገር ተረካቢ ትውልዶች አንድነትና ቀጣይነት የተመቻቸች እንዲትሆን አረንጓዴ አሻራችንን በደማቅ እንፅፋለን! ችግኛችን መትከልና መንከባከብ ለነገ ሀገር ተረካቢ ትውልዶች መሰረት መጣል ነው! ለነገ ሀገር ተረካቢ ትውልዶች ነገያቸውን ዛሬ ሰርተን፤ ቀጣዩ ትውልድ ለቀጣዮቹ ትውልዶች መሰረት እንዲሆኑ አኛዎቹ ዛሬዎች ዛሬን ለነገ እንኑር!! አረንጓዴ አሻራችንን አያኖርን ፣ ችግሮቻችንን በሰላማዊ መንገድ እየፈታን #የኢትዮጵያን እድገት እና ብልፅግናን እናረጋግጣለን! #ኢትዮጵያን_እናልብሳት🌲🌲🌳#አረንጓዴ_አሻራ🌴🌳🌲#Green_Legacy🌲🌳 ሰላም ፣ ፍቅር፣ ልማትና ብልፅግና ለኢትዮጵያችን ይሁንልን!!! መልካም የስራ ቀን ተመኘን!@lideta prosperity party_ብልፅግና
“ከተደመርን በሁሉም መስኮች ኢትዮጵያዊያን ያሰብነውን ማሳካት እንደምንችል አምናለሁ፡፡ ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም ጀንበር ወጥታ እስክትገባ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ቤቱ አይውልም፡፡ በዕቅፍ ካለ ሕጻን፣ በድካም ካለ አረጋዊ፣ በአልጋ ከሚገኝ ታማሚ በስተቀር ቤቱ ማንም አይውልም፡፡ ምክንያቱም ይህ የፖለቲካ ጉዳይ አይደለም፤ የፓርቲ ፕሮግራምም አይደለም፤ የመንግሥት ጉዳይም አይደለም፡፡ ይህ የኢትዮጵያ ጉዳይ ነው፡፡ የምትለብሰው ኢትዮጵያ ናት፡፡ ትርፉም ከእኛ አልፎ ለዓለም የሚተርፍ ነው፡፡ ስለዚህም የእምነትና የባህል፣ የፖለቲካ ፓርቲና አስተሳሰብ፣ እድሜና ጾታ፣ የትምህርትና የኑሮ ደረጃ ሳይለየን ሐምሌ 10 ቀን ከጀንበር ቀድመን እንውጣ፡፡ ከጀንበር በኋላ እንመለሳን፡፡ ኢትዮጵያን አረንጓዴ እናለብሳለን፡፡” – የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር)
ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር ከ500 ሚሊዮን ችግኝ በላይ መትከል ችላለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከሁነቶች መከታተያ ክፍል ባደረሱት መልዕክት ከጠዋት 12 ሰአት እስከ ማታ 12 ስአት ድረስ በተካሄደው የችግኝተከላ መርሃ ግብር ከ500 ሚሊየን ችግኝ በላይ መተከል መቻሉን አስታውቋል።