cs

ብልፅግና የህዝብን ጥያቄ ሰምቶ ምላሽ የሚሰጥ ፓርቲ..!!

ከመስከረም ጀምሮ ለሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወሰነ

ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወስኗል፡፡

የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ፤ መንግሥት የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሀገር ዐቅም የሚፈቅደውን ርምጃ እየወሰደ ነው ብሏል፡፡

በዚህም ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት መወሰኑን አስታውቋል፡፡

በማሻሻያው ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 4 ሺህ 760 ወደ ብር 6 ሺህ እንዲያድግ ይደረጋል ነው ያለው።

ከፍተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 21 ሺህ 492 ወደ ብር 39 ሺህ እንዲያድግ ይደረጋል ብሏል።

የዲግሪ ተመራቂ መነሻ ደመወዝ ከብር 6 ሺህ 940 ወደ ብር 11 ሺህ 500 የሚሻሻል መሆኑን ገልጿል።

ከሲቪል ሰርቪስ ውጭ በተለያዩ ዘርፎች የተሠማሩ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝም ማሻሻያ እንደሚደረግበት አስታውቋል።

ይህ የደመወዝ ማስተካከያ ከ160 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት ጠይቋል ያለው ኮሚሽኑ፤ ይሄም ለደመወዝ የሚወጣውን ጠቅላላ ዓመታዊ የመንግሥት ወጪ 56ዐ ቢሊዮን ብር ያደርሰዋል ብሏል።

aa_prosperity

Lemi kura_prosperity

FB_IMG_1754238534818

ሌላ ስኬት !

ከ1521 በላይ ሱቆችን የያዘ ፣ በርካታ ዜጎች ዘላቂ የሥራ ዕድል ያገኙበት የሰዉ ሀብት ልማት፣ኮሪደር ልማት ፤ የዛሬው ስኬት ነገም ይቀጥላላ….!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

FB_IMG_1754224444383

የሁለተኛው ዙር ኮሪደር ልማት አካል የሆነውና ዛሬ የተመረቀዉ ከ4 ኪሎ እስከ እንጦጦ ኮሪደር ፕሮጀክቶች ምን አካቶ ይሆን?

•ፕሮጀክቱ በአገሪቱ ዘመናዊ የአገር ግንባታ ሂደት ከፍተኛ ሚና ያላቸው ተቋማት የሚገኙበት ነዉ

•የህዝብ እንደራሴዎች መቀመጫ

•የምሁራን አምባ የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መገኛ ፣

•በአገሪቱ የመጀመሪያው የህክምና ተቋም የካቲት 12 ዘመናዊ ሆስፒታል መገኛ

•የመጀመሪያው የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት ሙዚየሞችና የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማትና እንዲሁም የከተማዋ የእደ ጥበብ ውጤቶች ልህቀት ማዕከል የሆነው ሽሮሜዳ መገኛ

•በአጠቃላይ በርካታ ግዙፍ መንግስታዊና ታሪካዊ ተቋማት የሚገኙበት መስመር የሚሸፍን እና 314 ሄክታር ስፋት ያለው መሬት ለምቷል

  • ቀድሞ 32 ሜትር ወደ 42 ሜትር መንገዱ ሰፍቷል
  • 3 ሜትር ስፋት ያለው የብስከሌት መንገድ
  • 11 የታክሲ እና የአውቶቡስ መጫኛና ማውረጃዎች
  • 20 አረንጓዴ ቦታዎች
  • 2 ፕላዛዎች
  • 10 ደረጃቸውን የጠበቁ የህጻናት መጫዎቻ
  • 7 ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች
  • 9 መጸዳጃ ቤቶች
  • ከ5-13 ሜትር ስፋት ያለው 11.4 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ
  • 2 (1 ዘመናዊ ሞልን ያካተተ በመንግስትና የግል አጋርነት እየተገነባ ያለ ተርሚናሎች እና 11 የታክሲ/ባስ መጫኛና ማውረጃዎች
  • 7 የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች
  • 417 ስማርት ፖሎች
  • ከ15 ሺ ለሚበልጡ ዜጎች ጊዚያዊ እና ቋሚ የስራ እድል
  • በአዲስ የተሰሩ 770 ሱቆች በመጨመር 1521 ሱቆች አካቷል
FB_IMG_1754224020643

አሳክተነዋልእናመሰግናለንለሚ_ኩራ!

ለመላው የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች ሐምል 24 ታላቅ ሀገራዊ ጥሪያችን ተቀብላችሁ ላደረጋችሁት አስደናቂ ተሳትፎ እያመሰገንን እንደ ክ/ከተማችን ትልቅ አሻራ አስቀምጠናል ዛሬ የተከልነው ችግኝ አንድም ጥላ አንድም ምግባችንን ነው በዚህ መርሀ ግብር ጥሪያችንን ተቀብላችሁ ለውጤት ያበቃችሁን ነዋሪዎቻችን በክ/ከተማችን ስም ላቅ ያለ ምስጋናችን ይድረሳችሁ🙏

በመትከል_ማንሰራራት

አረንጓዴዐሻራ

aa_prosperity

GreenLegacy

Lk_pp

FB_IMG_1754210345299

ስፖርት ለወንድማማችነት እና አብሮነትን ለማዳበር

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የቀጠለው በክፍለ ከተማ እና በወረዳ አመራሮች መካከል የሚደረገው የወዳጅነት የእግርኳስ ውድድር በዛሬው እለትም ተካሄዷል።

በዚህም የእግር ኳስ ጨዋታ መካሄዱ በዋናነት በአመራሩ መካከል ያለውን የወንድማማችነትን መንፈስን ለማዳበርና በአካል የዳበረና በስነ-ልቦናው ብቁ የሆነ አመራር ለመፍጠር አላማ ያደረግ መሆኑም ተገልጿል።

ሐምሌ 27/2017 ዓ.ም