በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም የገና በዓል ባዛር ዝግጅ የካ አቦዶ መስቀለኛ አደባባይ የከተማና ክፍለ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በይፋ ተከፍቷል ።
ባዛሩ ገበያን የማረጋጋትና ለአምርራች ኢንዳስትሪዎች የገበያ ትስስር የሚፈጥር ዓላማ በመያዝ በክፍለ ከተማው ስራ እና ክህሎት ፅ/ቤት ፣ ህብረት ስራና ኢንዱስትሪ ልማት ፅ/ቤቶች በቅንጅት መዘጋጀቱ ተገልጿል ።
ፕሮግራሙን መርቀው የከፈቱት የለሚ ኩራ ክፍለ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ እንደገለፁት በመጪው ገና በዓል የኢንዱስትሪናግብርና ምርቶችን በበቂ ሁኔታ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ከፍተኛ ዝግጅት መደረጉን ገልፀው ሸማቹ ህብረተሰብ ምርቶችን በጥራት በአቅራቢያቸው እንዲያገኙ የሚያስችል የተለያዩ መሸጫ ቦታዎች በማዘጋጀት የምርት አቅርቦቱ በብዛትና ጥራት እንዲቀርብ በክፍለ ከተማችን ያሉ የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራትና ዩኒየኖች ከክልሎች ዩኒየኖችና የገበሬ ህብረት ስራ ማህበራት ጋር የማስተሳሰር ስራ በመሰራት በዋናነት
ለበዓሉ የሚሆኑ ዶሮ፣እንቁላልና ሌሎች ምርቶች በስፋት የማቅረብ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል ።
በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍሰሐ ጥበቡ በመልክታቸው በመጪው ገና በዓል ገበያውን ለማረጋጋት እንደ ከተማ ሰፊ ዝግጅት መደረጉን ገልፀው አምራቾች ፣አርሶ አደሮችና ህብረት ስራ ማህበራትን በመጠቀም የግብርና ኢንደስትሪ ምርቶችን በስፋት በማቅረብ ገበያውን የማረጋጋት ስራ በስፋት ተስርቷል ብለዋል።
የገበያ መዳረሻዎችን የማስፋፋት ፣የምርት አቅርቦቱን የመጨመር እና ቁጥጥርና ክትትል ስራዎችን በማጠናከር በበዓሉ ወቅት ምንም አይነት የምርት እጥረት እንዳይኖር እየተሰራ መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል።
በመጨረሻም የለሚ ገበያ ማዕከል የግብርና እና ኢንዱስትሪ ምርቶች አቅርቦት ያለበት ደረጃ ጉብኝት አድርጓል ።
ለሚ ኩራ ኮሙኒኬሽን
ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም







