ከ1521 በላይ ሱቆችን የያዘ ፣ በርካታ ዜጎች ዘላቂ የሥራ ዕድል ያገኙበት የሰዉ ሀብት ልማት፣ኮሪደር ልማት ፤ የዛሬው ስኬት ነገም ይቀጥላላ….!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከ1521 በላይ ሱቆችን የያዘ ፣ በርካታ ዜጎች ዘላቂ የሥራ ዕድል ያገኙበት የሰዉ ሀብት ልማት፣ኮሪደር ልማት ፤ የዛሬው ስኬት ነገም ይቀጥላላ….!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
•ፕሮጀክቱ በአገሪቱ ዘመናዊ የአገር ግንባታ ሂደት ከፍተኛ ሚና ያላቸው ተቋማት የሚገኙበት ነዉ
•የህዝብ እንደራሴዎች መቀመጫ
•የምሁራን አምባ የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መገኛ ፣
•በአገሪቱ የመጀመሪያው የህክምና ተቋም የካቲት 12 ዘመናዊ ሆስፒታል መገኛ
•የመጀመሪያው የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት ሙዚየሞችና የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማትና እንዲሁም የከተማዋ የእደ ጥበብ ውጤቶች ልህቀት ማዕከል የሆነው ሽሮሜዳ መገኛ
•በአጠቃላይ በርካታ ግዙፍ መንግስታዊና ታሪካዊ ተቋማት የሚገኙበት መስመር የሚሸፍን እና 314 ሄክታር ስፋት ያለው መሬት ለምቷል
ለመላው የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች ሐምል 24 ታላቅ ሀገራዊ ጥሪያችን ተቀብላችሁ ላደረጋችሁት አስደናቂ ተሳትፎ እያመሰገንን እንደ ክ/ከተማችን ትልቅ አሻራ አስቀምጠናል ዛሬ የተከልነው ችግኝ አንድም ጥላ አንድም ምግባችንን ነው በዚህ መርሀ ግብር ጥሪያችንን ተቀብላችሁ ለውጤት ያበቃችሁን ነዋሪዎቻችን በክ/ከተማችን ስም ላቅ ያለ ምስጋናችን ይድረሳችሁ🙏
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የቀጠለው በክፍለ ከተማ እና በወረዳ አመራሮች መካከል የሚደረገው የወዳጅነት የእግርኳስ ውድድር በዛሬው እለትም ተካሄዷል።
በዚህም የእግር ኳስ ጨዋታ መካሄዱ በዋናነት በአመራሩ መካከል ያለውን የወንድማማችነትን መንፈስን ለማዳበርና በአካል የዳበረና በስነ-ልቦናው ብቁ የሆነ አመራር ለመፍጠር አላማ ያደረግ መሆኑም ተገልጿል።
ሐምሌ 27/2017 ዓ.ም
ለፀጥታ አካሉ የበሬ ስጦታ ያበረከቱት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ የሠላምና ፀጥታው አካል በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሠላም እንዲጠናቀቅ እያደረጉ ያለው ተግባር እጅግ የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው በዓሉ የሠላምና የደስታ እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
የለሚ ኩራ ኮሚኒኬሽን
ታህሳስ 28/2017 ዓ.ም









በእለቱ በስፍራው በመገኘት የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብሩን ያስጀመሩት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ እንዳሉት በዓሉ የአንድነት የፍቅር የመተሳሰብ የአብሮነት እንዲሆን እየተመኘው ያላችሁን ማንኛውንም ጥያቄዎች የክፍለ ከተማ አስተዳደሩ ደረጃ በደረጃ ፈጣን ምላሽ እንደሚሠጥም ገልፀዋል።
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፈንታሁን ሌማንቾ አክለው በዓሉን በእህታማማችነትና ወንድማማችነት መንፈስ ያለንን እየተጓደስ በጋራ እየተባበርን በአንድነት በዓሉ እናክብር ሲሉ መልካም የገና በዓልም እንዲሁም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
የለሚ ኩራ ኮሚኒኬሽን
ታህሳስ 28/2017 ዓ.ም





በምዘናው በተግባራት አፈፃፀም የታዩ ጥንካሬዎችን የማስቀጠልና ክፍተቶችን በማረም ለተሻለ ውጤታማ ስራ እውን መሆን አቅም ለመፍጠር ያለመ እንደሆነም ተገልጿል።
የለሚ ኩራ ኮሚኒኬሽን
ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም



የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የስራ ዕድል ፈጠራ፣ የልማት ትሩፋት የንቅናቄ ስራ እና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ቀጣይ በሚተገበረው የምግብ ዋስትና ፕሮግራም የተጠቃሚዎች ልየታ፣ የደረጃ ፍረጃ እና የ2ኛ ዙር ተጠቃሚዎች ምርቃት ተገምግሞ የስራ አቅጣጫ ማስቀመጡንም ገልጿል።
መድረኩን የመሩት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፈንታሁን ሌማንቾ እንዳሉት ተግባራቱን አመራሩ ትኩረት በመስጠት በከፍተኛ እርብርብና ቅንጅት ሊሠራ ይገባል ሲሉ አክለው አመራሩ የተለያዩ የንቅናቄ እና ሰው ተኮር ስራዎችን አቀናጅቶ የመምራት አቅሙን ተጠቅሞ ወጣቶችን ሴቶችን እና ሌላውን የህብረተሰብ ክፍል በማሳተፍ የሌማት ትሩፋት ስራውን በከፍተኛ እርብርብ መስራት ይኖርበታልም ብለዋል።
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ልመንህ ምህረቱ አክለው እንዳሉት ከሥራ ዕድል ፈጠራና ከሌማት ቱሩፋት የንቅናቄ ሥራዎች አንፃር የአፈፃፀም ሂደቱን አጠናክሮ መቀጠል ጥራቱን በሱፐርቪዥንና ድጋፍ በማድረግ ሥራዎችን ተሳስሮ እንዲቀጥል የአመራር ትኩረት ይፈልጋል ሲሉ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ተግባራዊ በሚደረገው የከተማ ምግብ ዋስትና እና ልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎችን ለመለየት የምዝገባ ሥራው መጠናቀቁ በመድረኩ በጠንካራ ጎን የተነሳ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናት ተመዝጋቢዎችን በደረጃ የመፈረጅ ሥራውን በማጠናቀቅ ለማህበረሰቡ ማስተቸት እንደሚገባ አቅጣጫ ሠጥተዋል።
የለሚ ኩራ ኮሚኒኬሽን
ታህሳስ 13/2017 ዓ.ም


የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት የሴት አመራሮችን አቅም ለማጎልበት በሴቶች ውሳኔ ሰጭነት እና የአመራር ብቃት ስልጠና መሰጠቱ ተገልጿል፡፡
በመድረኩ ላይ ተገኝተው የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሪት ወይንሸት አስናቀ ስልጠናው ጥሩ መነሳሳና ቁጭትን የሚያጭር ነው ያሉ ሲሆን የሰለጠነውን ስልጠና ወደ ተግባር ቀይረን በህይወታችን ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ሙሉ እመቤት ስራህ ብዙ የሴቶችን የአመራርና የውሳኔ ሰጭነት አቅም ለማጎልበት ከተቀመጡ የልማትና የለውጥ ፓኬጆች አንዱ የሴቶችን ውሳኔ ሰጭነትና የአመራር ብቃት ማሳደግ መሆኑን ገልጸው በሴቶች ውሳኔ ሰጭነት እና የአመራር ሚና ዙሪያ ከወረዳ እስከ ክ/ከተማ ለሚገኙ ሴት አመራሮች ስልጠና መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡
ወ/ሮ ሙሉእመቤት ሴቶች የሀገር ዋልታና መሰረት በመሆናቸው በተለያየ ደረጃ በሚገኙ የአመራርነት ማዕቀፎች ማሳተፍ እና የአመለካከት ለውጥ ማምጣት ሲቻል መሆኑን ገልጸው ሴቶች ከቤተሰብ ጀምሮ በየትኛውም የስልጣን ደረጃ መሳተፍ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
via ለሚ ኩራ ኮሚዩኒኬሽን
ታህሳስ 22/2017


በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ፅ/ቤት ከክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ጋር በመሆኑ ህብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነት /እህታማማችነት ለሁለንተናዊ ብልፅግና ” በሚል መሪ ቃል ከመምህራን ጋር የፓናል ውይይት አካሂዷል
በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ እንደተናገሩት መምህራን ሀገርን በመገንባት ሂደት ዋጋቸው ከፍ ያለና ትውልድን በእውቀትና በመልካም ስነ -ምግባር በመገንባት ትልቅ ሚና እንዳላቸው በመግለፅ የመድረኩ ተሳታፊዎች ገዥ ትርክት ህዝቦችን ከህዝቦች የሚያቀራርብ መሆኑን መገንዘብ ፣ህብረ -ብሔራዊ ወንድማማችነት/እህታማማችነት ያለውን ፋይዳ መረዳትና ለትውልድ በደንብ ማስተማር ለሀገር እድገት እና ብልፅግና በጋራ መቆም እንዲሁም የተጀመረውን ዜጎችን በጥሩ ስነ-ምግባር የመገንባት ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥሉ አሳስበዋል ።
የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ሌማንቾ በበኩላቸው ብልፅግና ጉዞአችን ለማፅናት ገዥ ትርክት አስፈላጊ በመሆኑ በትውልድ ግንባታ ላይ ከፍተኛ ሚና ያላቸው መምህራን በአሰባሳቢ ትርክት ዙሪያ ያለውን ግንዛቤ ከፍ በማድረግ ሀገርን በጋራ ለመገንባት በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
ለፓናል ውይይት መነሻ ፅሑፍ ያቀረቡት በብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ /ጽ/ቤት ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳዊት ምንዳዬ እንደገለፁት ገዢ ትርክት አሳባሳቢ፣ አብሮነታችንን የሚያፀና ፣ብሔራዊነት ለሁሉም እኩል ዕድል ፣በአስተሳሳሪ ነገ ላይ መገንባት የሚሰጥ ስለሆነ ገዢ ትርክትን በማፅናት መምህራን በትልውድ ግንባታ ላይ ያላቸውን አዎንታዊ ሚና መወጣት ያስፈልጋል ብለዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው መድረኩ በጣም አስፈላጊና ህብረ -ብሔራዊ ወንድማማችነት /እህታማማችነት እሴት የበለጠ ለማጠናከር የተሻለ ግንዛቤ ያገኙበት መሆኑን ገልፀው በቀጣይም የጋራ ግንዛቤ የሚያስጨብጡን ተመሳሳይ መድረኮች መዘጋጀት ይገባል ብለዋል።
ለሚ ኩራ ኮሙኒኬሽን
ታህሳስ 19/2017 ዓ.ም


