እንኳን ደህና መጡ መልዕክት!
F5fut1QXwAAUfSL

አገራችን ኢትዮጵያ የብዝሃነት ምልክትና የተለያዩ ማንነቶችን፣ እምነቶችን፣ ባህሎችን፣ ቋንቋዎችን፣ የፖለቲካ አስተሳሰቦችን አንድ ያደረገች አገር ነች። ዜጎቿ በብዝሃነት ቢለያዩም ልዩነታቸውን ውበታቸው በማድረግ ተከባብረውና ተቻችለው ለዘመናት ኖረዋል። በመሥዋዕትነት የአገራቸውን ሉዓላዊነትና ነፃነት ጠብቀው ለእኛ አስተላልፈዋል።

ሀገራዊ ለውጡን የወለደው የብልጽግና ፓርቲ የሀገራችንን ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስብራት በዘላቂነት መፍታት የሚቻለው አገራዊ አንድነታችንን በሚያጠናክርና በወንድማማችነት/በእህትማማችነት ማዕቀፍ ውስጥ በማየት ሁሉን አቀፍና ዴሞክራሲያዊ መፍትሄ ማምጣት እንደሚቻል በፅኑ ያምናል። ስለዚህ አገራዊ አንድነታችን በሕግ፣ በአሠራርና በተቋም ደረጃ ዋና አጀንዳ ሆኗል።

እኛም የ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ህዝቡ የጣለበትን ሃላፊነትና አደራ ከሁላችን በሁላችን ለሁላችን በሚል መርህ ፍጹም አካታችና አሳታፊ በሆነ መልኩ በብቃት እየተወጣ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ ተግቶ የሚሰራ መሆኑን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን።

ብልጽግና የሁሉንም ትብብርና ድጋፍ የሚሻ የመለወጥ፤የማደግና ከኃያላኑ ተርታ የመሰለፍ ጉዞ ነው፡፡ ይህ አድካሚ ጉዞ በግል በመሮጥ ብቻ የሚሳካ አይደለም፡፡ ብልጽግና ሊሳካ ከሆነ የጋራችን ርብርብ የግድ ይላል፡፡