የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የስራ ዕድል ፈጠራ፣ የልማት ትሩፋት የንቅናቄ ስራ እና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ቀጣይ በሚተገበረው የምግብ ዋስትና ፕሮግራም የተጠቃሚዎች ልየታ፣ የደረጃ ፍረጃ እና የ2ኛ ዙር ተጠቃሚዎች ምርቃት ተገምግሞ የስራ አቅጣጫ ማስቀመጡንም ገልጿል።
መድረኩን የመሩት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፈንታሁን ሌማንቾ እንዳሉት ተግባራቱን አመራሩ ትኩረት በመስጠት በከፍተኛ እርብርብና ቅንጅት ሊሠራ ይገባል ሲሉ አክለው አመራሩ የተለያዩ የንቅናቄ እና ሰው ተኮር ስራዎችን አቀናጅቶ የመምራት አቅሙን ተጠቅሞ ወጣቶችን ሴቶችን እና ሌላውን የህብረተሰብ ክፍል በማሳተፍ የሌማት ትሩፋት ስራውን በከፍተኛ እርብርብ መስራት ይኖርበታልም ብለዋል።
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ልመንህ ምህረቱ አክለው እንዳሉት ከሥራ ዕድል ፈጠራና ከሌማት ቱሩፋት የንቅናቄ ሥራዎች አንፃር የአፈፃፀም ሂደቱን አጠናክሮ መቀጠል ጥራቱን በሱፐርቪዥንና ድጋፍ በማድረግ ሥራዎችን ተሳስሮ እንዲቀጥል የአመራር ትኩረት ይፈልጋል ሲሉ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ተግባራዊ በሚደረገው የከተማ ምግብ ዋስትና እና ልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎችን ለመለየት የምዝገባ ሥራው መጠናቀቁ በመድረኩ በጠንካራ ጎን የተነሳ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናት ተመዝጋቢዎችን በደረጃ የመፈረጅ ሥራውን በማጠናቀቅ ለማህበረሰቡ ማስተቸት እንደሚገባ አቅጣጫ ሠጥተዋል።
የለሚ ኩራ ኮሚኒኬሽን
ታህሳስ 13/2017 ዓ.ም


Add a Comment