ለሴት አመራሮች የውሳኔ ሰጭነት እና የአመራርነት ሚና ስልጠና ተሰጠ፡

የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት የሴት አመራሮችን አቅም ለማጎልበት በሴቶች ውሳኔ ሰጭነት እና የአመራር ብቃት ስልጠና መሰጠቱ ተገልጿል፡፡

በመድረኩ ላይ ተገኝተው የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሪት ወይንሸት አስናቀ ስልጠናው ጥሩ መነሳሳና ቁጭትን የሚያጭር ነው ያሉ ሲሆን የሰለጠነውን ስልጠና ወደ ተግባር ቀይረን በህይወታችን ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ሙሉ እመቤት ስራህ ብዙ የሴቶችን የአመራርና የውሳኔ ሰጭነት አቅም ለማጎልበት ከተቀመጡ የልማትና የለውጥ ፓኬጆች አንዱ የሴቶችን ውሳኔ ሰጭነትና የአመራር ብቃት ማሳደግ መሆኑን ገልጸው በሴቶች ውሳኔ ሰጭነት እና የአመራር ሚና ዙሪያ ከወረዳ እስከ ክ/ከተማ ለሚገኙ ሴት አመራሮች ስልጠና መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡

ወ/ሮ ሙሉእመቤት ሴቶች የሀገር ዋልታና መሰረት በመሆናቸው በተለያየ ደረጃ በሚገኙ የአመራርነት ማዕቀፎች ማሳተፍ እና የአመለካከት ለውጥ ማምጣት ሲቻል መሆኑን ገልጸው ሴቶች ከቤተሰብ ጀምሮ በየትኛውም የስልጣን ደረጃ መሳተፍ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

via ለሚ ኩራ ኮሚዩኒኬሽን
ታህሳስ 22/2017

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *