‘ህብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነት /እህታማማችነት ለሁለንተናዊ ብልፅግና ”

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ፅ/ቤት ከክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ጋር በመሆኑ ህብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነት /እህታማማችነት ለሁለንተናዊ ብልፅግና ” በሚል መሪ ቃል ከመምህራን ጋር የፓናል ውይይት አካሂዷል

በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ እንደተናገሩት መምህራን ሀገርን በመገንባት ሂደት ዋጋቸው ከፍ ያለና ትውልድን በእውቀትና በመልካም ስነ -ምግባር በመገንባት ትልቅ ሚና እንዳላቸው በመግለፅ የመድረኩ ተሳታፊዎች ገዥ ትርክት ህዝቦችን ከህዝቦች የሚያቀራርብ መሆኑን መገንዘብ ፣ህብረ -ብሔራዊ ወንድማማችነት/እህታማማችነት ያለውን ፋይዳ መረዳትና ለትውልድ በደንብ ማስተማር ለሀገር እድገት እና ብልፅግና በጋራ መቆም እንዲሁም የተጀመረውን ዜጎችን በጥሩ ስነ-ምግባር የመገንባት ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥሉ አሳስበዋል ።

የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ሌማንቾ በበኩላቸው ብልፅግና ጉዞአችን ለማፅናት ገዥ ትርክት አስፈላጊ በመሆኑ በትውልድ ግንባታ ላይ ከፍተኛ ሚና ያላቸው መምህራን በአሰባሳቢ ትርክት ዙሪያ ያለውን ግንዛቤ ከፍ በማድረግ ሀገርን በጋራ ለመገንባት በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ለፓናል ውይይት መነሻ ፅሑፍ ያቀረቡት በብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ /ጽ/ቤት ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳዊት ምንዳዬ እንደገለፁት ገዢ ትርክት አሳባሳቢ፣ አብሮነታችንን የሚያፀና ፣ብሔራዊነት ለሁሉም እኩል ዕድል ፣በአስተሳሳሪ ነገ ላይ መገንባት የሚሰጥ ስለሆነ ገዢ ትርክትን በማፅናት መምህራን በትልውድ ግንባታ ላይ ያላቸውን አዎንታዊ ሚና መወጣት ያስፈልጋል ብለዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው መድረኩ በጣም አስፈላጊና ህብረ -ብሔራዊ ወንድማማችነት /እህታማማችነት እሴት የበለጠ ለማጠናከር የተሻለ ግንዛቤ ያገኙበት መሆኑን ገልፀው በቀጣይም የጋራ ግንዛቤ የሚያስጨብጡን ተመሳሳይ መድረኮች መዘጋጀት ይገባል ብለዋል።

ለሚ ኩራ ኮሙኒኬሽን
ታህሳስ 19/2017 ዓ.ም

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *