“ከተደመርን በሁሉም መስኮች ኢትዮጵያዊያን ያሰብነውን ማሳካት እንደምንችል አምናለሁ፡፡ ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም ጀንበር ወጥታ እስክትገባ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ቤቱ አይውልም፡፡ በዕቅፍ ካለ ሕጻን፣ በድካም ካለ አረጋዊ፣ በአልጋ ከሚገኝ ታማሚ በስተቀር ቤቱ ማንም አይውልም፡፡ ምክንያቱም ይህ የፖለቲካ ጉዳይ አይደለም፤ የፓርቲ ፕሮግራምም አይደለም፤ የመንግሥት ጉዳይም አይደለም፡፡ ይህ የኢትዮጵያ ጉዳይ ነው፡፡ የምትለብሰው ኢትዮጵያ ናት፡፡ ትርፉም ከእኛ አልፎ ለዓለም የሚተርፍ ነው፡፡ ስለዚህም የእምነትና የባህል፣ የፖለቲካ ፓርቲና አስተሳሰብ፣ እድሜና ጾታ፣ የትምህርትና የኑሮ ደረጃ ሳይለየን ሐምሌ 10 ቀን ከጀንበር ቀድመን እንውጣ፡፡ ከጀንበር በኋላ እንመለሳን፡፡ ኢትዮጵያን አረንጓዴ እናለብሳለን፡፡” – የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር)
Add a Comment